የፍቅር እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን የሲዳማ ህዝብ "ዳዮኤ ቡሹ" ለማስተዋወቅ እየተሰራ ነው

 


በቢሮው ድጋፍ የሚሰራው "የዳዎኤ ቡሹ ፊልም የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይም የተገኙት የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጃጎ አገኘሁ የፍቅር እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን የሲዳማ ህዝብን "ዳዮኤ ቡሹ" ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
የፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጅ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ፊልሙን በአጭር ቀናት ውስጥ ሰርቶ ለማጠናቀቅ እና ቢሮው የሰጠውን ሃለፊነት ለመወጣት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የፊልሙ ተዋናዮችም ፊልሙ ላይ ለመሳተፍ በመመረጣቸው ደስታ እንደተሰማቸውና የሲዳማን እምቅ ባህልን በሙያቸው ቀሚመው ለማስተዋወቅ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።
በፊልሙ ላይም በተወዳጅ 9ኛው ሺ ተከታታይ ድራማ ላይ የምናውቃቸው ተወዳጅ ተዋናዮች አርቲስት አበበ ተምትም ፣ አርቲስት ስናፍቅሽ ተስፋዬ እንዲሁም በተለያዩ ፊልሞች ላይ የምናውቀው አርቲስት ፈለቀ ካሳ እንዲሁም ከ50 የሚበልጡ ተዋናዮች እንደሚሳተፉበት ታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት