ይቅርታ መጠየቅ ተጠያቂነትን ያስቀራልን
በእርግጥ፣ በሲዳማ ውስጥ ባለፉት ሰባት ዓመታት ትልቅ የፖለቲካና የማኅበራዊ ለውጥ ተከስቷል። በዚህ የሰባት ዓመት የቀድሞ አመራር ዘመን የተነሱ የሥራ ዕድል፣ የፍትሕ፣ የተሳትፎና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ አግኝተዋል ወይስ አላገኙም የሚለው እንደየአተያዩ ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች ሊስማሙበት የሚችሉት አንድ ጉዳይ ቢኖር፣ ከመልካም አስተዳደር አንፃር የታዩ እና የክልሉን የዲሞክራሲያዊ እድገት ያደናቀፉ አሰራሮች፣ ሕዝባዊ ጥያቄዎችን የማፈን፣ የመናቅ እና አሳንሶ የማየት አባዜ የአመራሩ ባህል ሆኖ መቆየቱ ነው። በዚህም ሕዝቡ ቅሬታውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጽ ቆይቷል፤ ሰሚ ባያገኝም። በዚህ አውድ፣ እኚህ የቀድሞ አመራር ሥልጣናቸውን ሲለቁ ከሕዝብ ይቅርታ መጠየቃቸው በራሱ አንድ አዎንታዊ የሞራል እርምጃ ሊሆን ይችላል። ግን ይቅርታ መጠየቅ ተጠያቂነትን አያስቀርም። በተቃራኒው፣ እውነተኛ ይቅርታ ወደ ተጠያቂነት የሚወስድ መነሻ መንገድ መሆን አለበት። ይቅርታ እና ተጠያቂነት አንድ ነገር አይደሉም። ይቅርታ ጸጸትን መግለጽ ሲሆን፣ ተጠያቂነት ግን ምን እንደተፈጠረ፣ ለምን እንደተፈጠረ እና የማን ኃላፊነት እንደነበረ በማስረጃ መመርመር ነው። ሕግ የተጣሰበት ጉዳይ ካለም፣ ይቅርታ የሕግን ሂደት ሊተካ አይችልም። ተጠያቂነት ማለት በቀል ሳይሆን፣ እውነትን መፈለግና ፍትሕን ማረጋገጥ ነው። በሲዳማ ውስጥ የወጣቶች ድምፅ እና ጥያቄ በተለይ ትኩረት ይፈልጋል። ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ጥያቄና ቅሬታቸውን መግለጻቸው ችግርን በራሱ አይፈታም፤ ነገር ግን ድምፃቸውን የማሰማት አንዱ መንገድ ነው። እኚ አመራሪ፣ በአመራር ጊዜያቸው ወጣቶች በፌስቡክ ላይ የሚጽፉትን ጥያቄና ቅሬታ “ምንም ነገር አያመጣም” በሚል አመለካከት መመልከታቸው፣ እና ዛሬ ይቅርታ ከመጠ...