በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ
በባህርዳር ከተማ ተገኝተው ልምዱን ያካፈሉት “የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ም/ሀላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል ሲሆኑ:- እንደ ሲዳማ ብሔር ይህ ቱባ ባህል የከበረ ባህል ሲሆን ዕድሜ ጠገብና እጅግ የሚያኮራ እንዲሁም ለዕርቅና ለሰላም ግንባታ ትልቅ ሚና ያለው ባህል ብለዋል።
"አፊኒ" ትልቅ የሀገር እሴት መሆኑንና ይህንንም ባህላዊ የዳኝነት ስርአትን የሚደግፍ የማህበረሰብ ፍትህ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚረዳ አዋጅ በሲዳማ ክልል ምክር ቤቱ እንዳፀደቀ ገልፀዋል::
በመድረኩ የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሐን, የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ ክብርት ፋንቱ ተስፋዬና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አለምአንተ አግደዉ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል::
የማህበረስብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ሚናን አስመልክቶ የሲዳማ ብሔር "አፊኒ" ባህላዊ ዳኝነት ስርዓትና ተሞክሮን በተመለከተ ህብረተሰቡ ዘመናዊ የዳኝነት ስርዓትን በማይቃረን መልኩ ሳይጉላላና ለአላስፈላጊ ወጪ ሳይዳረግ ፍትህ እንዲያገኝ በማሰብ እየተሰራ ያለ መሆኑ ተገልፆአል::
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የተዘጋጀው መድረክ ላይ ክልሉ የራሱን የረቂቅ ሞዴል ህግ እንዲሁም ሌሎች የጥናት ጽሁፎችና የኦሮሚያ ክልል ልምድም ቀርቦ በሀገር ሽማግሌዎች: የሐይማኖት አባቶችና ምሁራን ሠፊ ውይይት ተደርጎአል።
የባህል ፍርድ ቤቶችን ስለማቋቋምና እዉቅና ስለመስጠት፣ የባህላዊ ግጭት መፍቻ ዘዴዎች ዳሰሳ መደረጉ ስርአቱን ለማጠንከር ማህበረሰዋዊና ብሎም ሀገራዊ ሰላምን አብሮነትን የሚያጠነክር መሆኑም ተነስቶ ከሲዳማና ከኦሮሚያ ክልል ለቀረቡ ልምዶች ላቅ ያለ ምስጋና ተችሮአል::
Comments
Post a Comment