የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

May be an image of 2 people, airplane, outdoors and text that says 'c ASTA STAFRICAN RICAN AVIA AVIATION FASTAFRICANAVIATION ION FT-ATE' 

ከሰሞኑ አንዳንድ የስራ ሀላፊዎች የቻርተር አውሮፕላን በረራዎችን ደጋግመው ሲጠቀሙ ተመልክተናል። ታድያ እነዚህ በአንድ ጉዞ ብቻ የመቶ ሺህ ብሮችን ወጪ የሚጠይቁ በረራዎች የተካሄዱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ በረራ ጠፍቶ ወይስ በምን አግባብ ይሆን?

በግሌ ለማየት እንደሞከርኩት በነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ነበሩ። ለምሳሌ ባለፈው አርብ የሲዳማ ክልል ፕሬዝደንት የሚድሮክን King Air 360 ቻርተር አውሮፕላን በተጠቀሙበት እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET228 ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ በረራ ነበረው፣ ሌሎቹም እንዲሁ።
እርግጥ ነው እንደ ቡህታን ንጉስ ያሉ ቢሊየነሮች አይደለም የቻርተር በረራ የራሳቸው ግዙፍ አውሮፕላን አላቸው። ነገር ግን ተጠያቂነት ባለባቸው ሀገራት ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲህ አይነት አሰራር አይታሰብም። በአንድ ወቅት የአሜሪካው ሴናተር ቴድ ክሩዝ በመንገደኛ አውሮፕላን ከህዝብ ጋር ተሳፍረው ሳለ ያጋጠማቸውን ሰምታችሁ/አንብባችሁ ይሆናል።
ጦርነት፣ ድርቅ እንዲሁም ሌሎች ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ከፍተኛ ጫና ሀገር ላይ እያደረሱ ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ጉዞዎች ተገቢ ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ?
 
ኤሊያስ መሰረት  

Comments

  1. The Casinos of Las Vegas - PBS Jane's
    The 윈윈 벳 먹튀 Casino of Las Vegas · Bellagio Hotel 벳 페어 and Casino · 바카라프로그램 Encore Boston Harbor · The Bellagio seda bet Hotel and Casino · Wynn Hotel & Casino · Encore 사이트추천 Boston

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት