9ኛው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የ2017ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ውድድር በሀዋሳ ከተማ እሁድ ታህሳስ 6 እንደሚጀመር ተገለፀ።


በሀገራችን ካሉ ስኬታማ እና ውስን ፕሪሚየር ሊጎች ከግንባር ቀደሞቹ ተርታ የሚገኘው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የ2017ዓ.ም መርሀ-ግብር ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል።

ውድድሩ በ10 ክለቦች መካከል የሚካሄድ ሲሆን የመቻል፣ የኦሜድላ፣ የፌደራል ማረሚያ፣ የቂርቆስ፣ የኮልፌ ቀራንዮ፣ የመቀሌ 70 እንደርታ፣ የከንባታ ዱራሜ፣ የፋሲል ከነማ፣ የሚዛን አማን እና የባህር ዳር ከነማ እጅ ኳስ ክለብ ይሳተፋበታል።

ውድድሩ በሀዋሳ፣ በአዲስ አበባ እና በተመረጡ የሀገራች ከተሞች አመቱን ሙሉ የሚካሄድ ሲሆን መክፈቻ ፕሮግራሙ እሁድ ታህሳስ 6, 2017ዓ.ም የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይካሄዳል ሲሉ የፌዴሬሽኑ እና የምስራቅ አፍሪካ ዞን 5 ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደ ሰንበት አሳወቀዋል።

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!