የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!
ከሰሞኑ አንዳንድ የስራ ሀላፊዎች የቻርተር አውሮፕላን በረራዎችን ደጋግመው ሲጠቀሙ ተመልክተናል። ታድያ እነዚህ በአንድ ጉዞ ብቻ የመቶ ሺህ ብሮችን ወጪ የሚጠይቁ በረራዎች የተካሄዱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ በረራ ጠፍቶ ወይስ በምን አግባብ ይሆን? በግሌ ለማየት እንደሞከርኩት በነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ነበሩ። ለምሳሌ ባለፈው አርብ የሲዳማ ክልል ፕሬዝደንት የሚድሮክን King Air 360 ቻርተር አውሮፕላን በተጠቀሙበት እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET228 ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ በረራ ነበረው፣ ሌሎቹም እንዲሁ። እርግጥ ነው እንደ ቡህታን ንጉስ ያሉ ቢሊየነሮች አይደለም የቻርተር በረራ የራሳቸው ግዙፍ አውሮፕላን አላቸው። ነገር ግን ተጠያቂነት ባለባቸው ሀገራት ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲህ አይነት አሰራር አይታሰብም። በአንድ ወቅት የአሜሪካው ሴናተር ቴድ ክሩዝ በመንገደኛ አውሮፕላን ከህዝብ ጋር ተሳፍረው ሳለ ያጋጠማቸውን ሰምታችሁ/አንብባችሁ ይሆናል። ጦርነት፣ ድርቅ እንዲሁም ሌሎች ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ከፍተኛ ጫና ሀገር ላይ እያደረሱ ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ጉዞዎች ተገቢ ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ? ኤሊያስ መሰረት
Comments
Post a Comment