ለፊቼ ጫማባላላ በዓል ወደሀዋሳ ከተማ ለሚመጡ እንግዶች ህብረተሰቡ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

ግንቦት 20/2011 ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ “ ፊቼ ጫማባላላ ” በዓል ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት ወደ ሃዋሳ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን የከተማዋ ነዋሪዎች በመልካም መስተንግዶ እንዲቀበሉ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ ጥሪ አቀረቡ፡፡
አቶ ስኳሬ በዓሉን አስመልክቶ ለመላው የሲዳማ ህዝብ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵውያ ን እንዲሁም መላውን የዓለም ህዝብ በራሳቸውና በከተማ አስተዳደር ስም የእንኳን አደረሳችው መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት በዓሉን ለማክበር ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችና “ፊቼ ጫማባላላ” ን ከሲዳማ ህዝብ ጋር ለማክበር የወደዱ በርካታ እንግዶች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ወደ ሀዋሳ ከተማ ይመጣሉ።
በመሆኑም የከተማዋ ነዋሪዎች በተለመደው መልካም መስተንግዶ እንግዶቻቸውን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የከተማዋን ጸጥታ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ከብሔሩ ወጣቶች ጋርም በዚህ ረገድ ቅንጅት መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡
በዓሉን በሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ከሲዳማ ህዝብ ጋር በጋራ የሚያከብሩት መሆኑንም አቶ ስኳሬ ተናግረዋል፡፡
የህዝቡን አንድነትና ትብብር የማይፈልጉ ኃይሎች የተለያዩ ትንኮሳዎችን በማካሄድ የበዓሉን ድባብ ለማደብዘዝ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቁመው የከተማው ህብረተሰብ ይህን ተረድቶ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና ለፀጥታ መዋቅር አካላት ጥቆማዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን አሳስበዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ