የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከነገ ጀምሮ መከበር ይጀምራል


አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡
የዋዜማ በዓሉ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ስነ ስርዓች በጎዳና ላይ በሀዋሳ ከተማ ተከብሮ ውሏል፡፡
በሲዳማ ብሔር ባህላዊ ጭፈራ“ቄጣላ ” እና በሌሎች ስነ ሰርዓቶች ነው በሃዋሳ ከተማ ጎዳናዎች የፊቼ ጫምባላላ ሲከበር የዋለው፡፡
በርካታ ባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች እንዳሉት የሚነገረው ፊቼ የሲዳማ ብሔር አንኳር የሆኑ ባህላዊ ገጽታዎች የሚንጸባረቁበት እንደሆነ ይነገራል፡፡
የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ የሚታወቅ ነው፡፡
በዓሉ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር ይጀምራል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ