ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በተገኘበት በሃዋሳው ጉዱማሌ የፍቼ ጫምባላላ በዓል እየተከበረ ነው
የፍቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ ጉዱማሌ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሀዋሳ ጉዱማሌ እየተከበረ ነው።
በዓሉን ለማክበር ከሲዳማ ዞን 32 ወረዳዎች፣ ከደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተወካዮች ተሳትፈውበታል።
የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ የሆነው በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት/ዩኔስኮ/ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበ ሦስት ዓመታትን አስቆጥሯል።
በበዓሉ ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ተሳታፊዎች መገኘታቸውም ተጠቅሷል።

Comments
Post a Comment