የፊቼ ጫምባላላ በዓል መከበር ጀምሯል



የፊቼ ጫምባላላ  በዓል በሃዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ግንቦት 22፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሃዋሳ ከተማ እተከበረ ነው።
ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በዛሬው ዕለት በሃዋሳ ከተማና በሌሎች አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
የፊቼ ጫምባላላ  በዓል እየተከበረ የሚገኘውም በዓሉን በሚያንፀባርቁ የተለያዩ ካርኒቫሎችና የጎዳና ላይ ትርኢቶች ነው።
ከዚህ ባለፈም በዓሉ  ፍቅር፣ አንድነትንና መተሳሰብን በሚያረጋግጥ መልኩ እተከበረ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ዛሬ በሚከናወነው የፊቼ ጫምባላላ  በዓል ስነ ስርዓት ላይም የሲዳማ ብሄር ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚዬም ይካሄዳል።
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ በትንንትነው ዕለት በተለያዩ ካርኒቫሎችና የጎዳና ላይ ትርኢቶች በሃወሳ ከተማ ተከብሯል።
በርካታ ባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች እንዳሉት የሚነገረው ፊቼ የሲዳማ ብሔር አንኳር የሆኑ ባህላዊ ገጽታዎች የሚንጸባረቁበት እንደሆነ ይነገራል፡፡
የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ የሚታወቅ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ