እንደ የጋሞ ሽማግሌዎች ሁሉ የወንዶ ገነት ኤጄቶዎች ለመላው አገሪቱ ምሳሌ የሚሆን ተግባር ፈጸሙ፤ ከፍተኛ የብሄር ግጭት አስቀሩ



በዛሬው አለት #በሲዳማ ክልል ወንዶገነት በተለምዶ ወተራ በሚባል አከባቢ፤ የአንድ ትምህርት ቤት ተማሪ በሆኑ እና በብሄራቸው የሲዳማ እና የጉጂ ኦሮሞ ቤተሰብ በሆኑ ልጆች መካከል በተፈጠረው አለማግባባት ወይም ጥል አንደኛው ልጅ ህይወቱ ሟቹ ብሔሩ ሲዳማ ስሆን፣ ገዳዩ የጉጂ ኦሮሞ በመሆኑ በላይ ክስተቱ የተከሰተው በድንገት ባጋጣሚ ቢሆንም ግቱ የብሔር መልክ ይዞ ወደ ብሔር ግጪት እንዳይለወጥ ኤጄቶ የማይረሳ መስዋዕትነት ከፍሎ በታላቅ ቁጣ የመጣውን የሟች ቤተሰብ አስፓልት ላይ በመምበርከክ ለምኖ በማረጋጋት ከትልቅ እልቂት ህዝቡን ልያድን ችሏል።

"የጋሞ ሽማግሌዎችን መልካም መሰል ተግባርን ተከትሎ ፤ ወጣቶች ዛሬም ባህላቸውን እንዳልረሱና ሽማግሌዎችን እንደሚሰሙ ሰውን ከመግደል ማቀፍ የሚሻል መሆኑን ባለመግደል ማሸነፍ መቻሉን፤ የወንዶ ገነት ኤጄቶዎች የጋሞን ሽማግሌዎችን ዱካ በመከተል ታላቅ ጅብድ በመስራት አሳይተዋል።

በተለይ ዛሬ ዛሬ በአገሪቱ በህዝቦች መካከል የሚታየው ቁርሾ እና ግጭት፣አገሪቱ የተተበተበችበት የዓመፃና የክፋት፣ የጥላቻና የጠላትነት እስራን፣ ሰንሰለን በጣጥሰው ነጻ የሚያወጡት ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ይቅርታን የሚሰብኩ የወንዶ ገነትን ኤጄቶዎች መሰል ወጣቶች እሰላም አምባሰደሮች ያስፈልጉል፡፡ እንደአገር፤ የትናንትና የአብሮነትና የአንድነት ውብ ታሪካችንን በቅጡ ፈትሸው ለመጠየቅና ይቅር ለመባባል፣ ለፍቅር፣ ለዕርቅ ልብ እንዲኖረን ዘንድ በተግባር ላሳዩን የወንዶ ገነት ኤጄቶዎ ታላቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡


የሲዳማ ክልላዊ መንግስት መመስረትን በታላቅ ትግእስት በመጠባበቂ ላይ ያለው የሲዳማ ህዝብ፤ ብሎም ለተግባራዊነቱ በመታገል ላይ ያለው ኤጄቶ፤ አገራችን የጀመረችው የለውጥ ሂደት የተሳካ እንዲሆን በመሰል ተግባራት ላይ በመሳተፍ የበኩሉን በመወጣት ላይ መሆኑ አድናቆትን ያስችራቸዋል።
#Sidama, #Ejjetto,#Wondogenet,#Oromo,#Oromogujje,#Gamo 

*ፎቶ ከመልካሙ ኢሳያስ


Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ