ወደ ውጪ ከሚላከው ቡና ገሚሱን ቆልቶ በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እየተሰራ ነው

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ወደ ውጪ ከምትልከው ቡና ግማሽ ያህሉን ሀገር ውስጥ ቆልታ በመላክ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን ተገለፀ።
ወደ ውጪ ከሚላከው ቡና ገሚሱን ቆልቶ በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እየተሰራ ነውየኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ልማት ግብይት ባለ ስልጣን በቡና ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የተጀመረ ቢሆንም፥ በቀጣይ ከሚመረተው ቡና 50 በመቶ ያህሉን እሴት ጨምሮ ለመላክ የሚያስችሉ ስራዎች ከወዲሁ እየተሰሩ ነው ብላዋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር የቡና ምርትን ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ የቡና አብቃይ አካባቢዎች እየተለዩ እንዳሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ 25 በመቶ የወጪ ንግዷ በቡና የሚሸፈን ሲሆን 708 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና እየለማ ነው። 
በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት 270 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም አቀፉ ገቢያ በማቅረብ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል።
ባለስልጣኑ የዘንድሮ እቅዱን ለማሳካት ዓለም አቀፍ የቡና አውደ ርእዮች ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያ ቡና ፈላጊ ሀገራት ቁጥርን ለማሳደግ እንደሚሰራ ማስታወቁን ይታወሳል።
 ባለፈው ዓመትም 225 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ቀርቦ 882 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱ ይታወቃል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር