ሲዳማ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛል ተባለ

Image result for sidamaበሚቀጥሉት አሥር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታ መኖሩን ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ።

ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ በኅዳር ወር ሊኖር የሚችለውን አገራዊ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ ትንበያን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በኤጀንሲው ትንበያ መሰረት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የበጋ ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በግብርና እንቅስቃሴ ላይ የሰብል ጥፋትና የምርት ብክነት ሊያስከትል ስለሚችል የደረሱ ሰብሎችን በአፋጣኝ መሰብሰብ፤ የተሰበሰቡትም ዝናብ በማያስገባ ሁኔታ መከመር እንደሚገባ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በሌላ በኩል የወቅቱ ዝናብ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ቀጣይነት እንደሚኖረው ነው የተመለከተው።

አልፎ አልፎ ባሉት ቀናትም ወቅታዊ ያልሆነ ዝናብ በአንዳንድ የሰሜን፣ የመካካለኛውና የምሥራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ይከሰታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ትንበያው ጠቁሟል።

በአብዛኛው የትግራይ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል አዊ ዞን፣ የባህር ዳር ዙሪያ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግ ኽምራ፣ የሰሜን ደቡብ ወሎ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

በተመሳሳይም ከኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ጉጂ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው በትንበያው ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ደረቅ የአየር ሁኔታ እያመዘነ ቢሆንም በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ሀረሪ፣ ድሬደዋና በአዲስ አበባ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

በተጨማሪም የቤኒሻንጉል ጉምዝና የጋምቤላ ሁሉም ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር በተቀራረበ የዝናብ መጠን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በአንፃሩ የአፋር 3 እና 5 ዞኖች በጥቂት ሥፍራዎቻቸው ዝናብ እንደሚስተዋልባቸው የትንበያው መረጃ ያሳያል።

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የከፋና የቤንች ማጂ ዞኖች፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሀዲያ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሲዳማ፣ ጋሞጎፋና የሰገን ህዝቦች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ።

በተመሳሳይ ሁኔታ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የጅግጅጋና የሲቲ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ትንበያው ያስረዳል።

በተቀሩት የሊበን፣ የአፍዴር፣ የጎዴ፣ የቆራሄ፣ የፊቅ፣ የደጋሀቡርና የዋርዴር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተለይም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችና በደቡብ ኦሮሚያ እንዲሁም በሶማሌ ክልሎች የሚጠበቀው ዝናብ በአንዳንድ ሥፍራዎች ላይ ከባድ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አልፎ አልፎ  ቅጽበታዊ ጎርፈ ሊከሰት እንደሚችል ነው ትንበያው ያመለከተው።

ከመደበኛ በላይ ከሆነ ዝናብ ጋር ተያይዞ ዕድገታቸውን ላልጨረሱ የመኸር ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች፣ ለከብቶች የመጠጥ ውኃና ለግጦሽ ሣር አቅርቦት ዝናቡ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
 - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/environment/item/8923-2015-11-04-18-40-54#sthash.LFCkyiyr.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር