በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጫዋታ ሀዋሳ ከነማ ድል ኣልቀናውም

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ዛሬ 10 ሰአት ላይ መከላከያና ሀዋሳ ከተማ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል።
በጨዋታውም መከላከያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
መከላከያ በመጀመሪያው አጋማሽ ምንይሉህ ወንድሙ እንዲሁም በሁለተኛው ግማሽ ፍሬው ሰለሞን ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ነው ማሸነፍ የቻለው።
በዚህም ክለቡ በሶስት አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን፥ በአጠቃላይም ለ12ኛ ጊዜ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።
ይህም የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ብዙ ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ክለብ ያደርገዋል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ጊዜ በማሸነፍ ይከተላል።
መከላከያ የጨዋታው አሸናፊ በመሆኑ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ይፎካከራል።
በመጭው መስከረም 23 ቀን ከአምናው የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታውን ያደርጋል።
ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኛነት መርተውታል።
- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/fbc-sport/item/10525-%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB-%E1%8B%A82007-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8C%A5%E1%88%8E-%E1%88%9B%E1%88%88%E1%8D%8D-%E1%8A%A0%E1%88%B8%E1%8A%93%E1%8D%8A-%E1%88%86%E1%8A%90.html#sthash.PIkEK4LD.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ