የአለታ ወንዶ- ዳዬ 51 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በዚህም መሰረት የሲዳማ ቡናን ወደ ማዕከላዊም ሆነ ወደ ዓለም ገበያ በማውጣት የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል፣ የንግድ ግንኙነትን ለማሳለጥ፣ የገበያ ትስስርን ለመፍጠርና በወረዳዎች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡ መንገዱ ኣምስት የሲዳማ ወረዳዎችን በተለይም የሁላ፣ የቦናን እና የበንሳ ወረዳዎችን ከዞኑ ዋና ከተማ ሃዋሳ ጋር ለማገናኘትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
በዕለቱም በ"ዳዬ" ከተማ ለሚገነባው የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። የካምፓሱ መገንባት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግና ጥራቱን ይበልጥ ለመጨመር የሚያስችሉ ምርምሮች እንዲካሄዱ ዕድል ይፈጥራል።
Comments
Post a Comment