የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ በሚያወጣው የአፍሪካ መልካም አስተዳደር ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ52 አገሮች 32ኛ ወጣች
ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች መካከል ሩዋንዳ በ11ኛ ደረጃ፣ ኬንያ 17ኛ ደረጃ፣ ኡጋንዳ 19ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ኢትዮጵያ 32ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ ሶማሊያ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስትገኝ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ኤርትራ ይከተሏታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ ለአፍሪካ መሪዎች የሚሰጠውን ሽልማት የሥልጣን ዘመናቸውን በማጠናቀቅ ላይ ለሚገኙት የናሚቢያው ፕሬዚዳንት አድርጓል፡፡ ይህ ሽልማት ላለፉት አራት ዓመታት ብቁ የሆነ መሪ ባለመገኘቱ ሳይካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ሽልማቱ በሥልጣን ላይ እያለ ለአገሩ መልካም አስተዳደር ላሰፈነ፣ የሕዝቦቹን የኑሮ ደረጃ ከፍ ላደረገና በሰላማዊ ሽግግር ከሥልጣን ለወረደ መሪ የሚሰጥ ነው፡፡ ሽልማቱም በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ አምስት ሚሊዮን ዶላርና እስከ ዕድሜ ልክ ደግሞ በየዓመቱ 200 ሺሕ ዶላር ያስገኛል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ሁለት የሥልጣን ጊዜያትን ያሳለፉት የናሚቢያው ፕሬዚዳንት ሂፈክፑንዬ ፓሃምባ፣ በቅርቡ በተደረገ ምርጫ ላሸነፉትና ገና ሥልጣን ላልተረከቡት ሄግ ጌንጐበ ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Comments
Post a Comment