ሃዋሳ ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 አሸነፈ
Photo from Social media |
በሃዋሳ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሃዋሳ ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
በጨዋታው በመጀመሪያው ግማሽ ሁለቱም ክለቦች ካለምንም ግብ እረፍት ቢወጡም በሁለተኛው አጋማሽ ሃዋሳ ከነማ አጥቅቶ በመጫወት ታፈሰ ሰለሞን በ75ኛው እንዲሁም ደስታ ዮሀንስ በ86ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ሁለት ጎሎች ሊያሸንፍ ችሏል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ሲዳማ ቡናና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ሲቀናቸው፥ ወላይታ ዲቻና መብራት ሀይል ተሸንፈዋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሲረከብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ 2ኛ፣ ወላይታ ዲቻ በ25 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
FBCየፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሲረከብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ 2ኛ፣ ወላይታ ዲቻ በ25 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
Comments
Post a Comment