ወገን ተወያይ!

እንደ
ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ1894 ኣም
ማለትም ከመቶ ኣመታት በፊት ከኣዲስ ኣበባ
ወደ ጅቡቲ ወደብ በተዘረጋው ባለ ኣንድ የባቡር
መስመር ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ ኣሮጌውን
የኣዲስ ኣበባ_ጅቡቲ
የባቡር መስመር በዘመናዊ መስመር ከመተከቷ
ባሻገር በኣምስት ኣመት የትራንስፎርሜሽን
ኣቅድ በሺዎች በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች መላዋን
የኣገርቱን ክልሎች ለማገናኘት ፕሮጄክት
ነድፋ ከመንቀሳቀሷ ላይ ናት።
ይህ
የኣገሪቷን ክልሎች ያገናኛል የተባለለት
የባቡር መስመር ዝርጋት ፕሮጄክት የትኛውንም
የሲዳማን ከተማ እና ኣከባቢን ኣይጨምርም። ለኣብነት ያህል ከኣዲስ ኣበባ ተነስቶ ወደ ሞያሌ የምዘልቀው የባቡር መስመር ሆነ ተብሎ በኣርባምንጭ_ኮንሶ ኣድርጎ እንድሄድ ተደርጓል።
ለመሆኑ
የባቡር መስመር ዝርታ ፕሮጄክቱ የሲዳማን
ኣከባቢዎች ያላከተተበት ምክንያት ምንድነው?
ወገን ተወያይ!
Comments
Post a Comment