ማጆ እና መንገዶቿ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ከትላልቅ ከተሞች ጀምሮ እስከ ትናንሾቹ ድረስ በመካሄድ ላይ ከምገኙት የከተማ ልማት ፕሮግራሞች መካከል ኣንዱ የከተሞችን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በኮብል ድንጋይ ንጣፍ ማልበስ ስራ ነው።
የዛሬ 10 እና 12 ኣመታት በፊት በድሬዳዋ ከተማ ተጀምሮ እንደሰደድ እሳት በመላዋ ኣገሪቱ የምገኙትን ከተሞች ያዳረሰው የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ለከተሞቹ ገጽታ መለወጥ ከፍተኛ ኣስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ነው። በሲዳማም ኣከባቢ በተለይ በሃዋሳ ከተማ የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራ ለበርካታዎቹ ስራ ኣጦች የስራ እድል ከፍቷል፤ ብሎም ከተማዋን ኣሳምሯታል።
በሌሎች የሲዳማ ከተሞችም በመካሄድ ላይ ያሉት እና የተካሄዱት የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራዎች ለየከተሞቹ ገጽታ መሻሻል እና ከነዋሪዎቻቸው የስራ እድል በመፍጠሩ በኩል እሰዬ የሚያስብሉ ናቸው።
ከዚህም ባሻገር በክረምት ወቅት በተለይ በይጋዓለም፤ ኣለታ ወንዶ ወይም በሌሎች የሲዳማ ከተሞች ይታዩ የነበሩት በጭቃ የተለወሱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ቁጥር እንድቀንስ ማድረግ ችሏል፤ ይህ የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራ።
Comments
Post a Comment