የይርጋለም ከተማ ወጣት መምህራን

መምህርት ሰብለ ሽፈራው እና መምህር ታምራት ታደሰ ትምህርት ቤት የወጣትነት ትውስታ ነው። አብዛኞቻችን ትምህርት ቤትን የመጀመሪያ የዕውቀት መቅሰሚያ አድርገን ትተን ወደ ተለያዩ የሙያ መስክ ስናመራ፤ አንዳንድ በፍላጎት አልያም በአጋጣሚ የመምህርነት ሞያን ይዘዉ ፤ በዝያዉ እዉቀትን በቀሰሙበት፤ ትምህርት ቤት ይቆያሉ።
Schüler in einem Dorf in Äthiopien
መምህርት ሰብለ ሽፈራው እና መምህር ታምራት ታደሰ ይባላሉ። ወጣት መምህራኑ እንደሚሉት አስተማሪ መሆን ሁሌም ምኞቻቸው ነበር።ታምራት የ9ኛ ክፍል የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው። ወደ ይርጋለም የሄደው በዚሁ በሥራ እድል ምክንያት ነው፤ ያደገው ግን ሐዋሳ ከተማ ነው። መምህርት ሰብለም እንዲሁ ከይርጋለም ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ በሚገኘው ትምህርት ቤት ውስጥ የ10ኛ ክፍል የባዮሎጂ መምህርት ናት።ወጣት መምህራኑ፤ ከከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ማስተማሩን እንደ ህዝባዊ ግዴታ ነው የሚቆጥሩት። በዚህም ደስተኛ ናቸው።

መምህራኑ ከሙያው የሚወዱት ነገር ምንድን ነው? አስተማሪነትስ ምን አይነት ኃላፊነት አለው? በመምህርነት ከሚያገለግሉት ሁለት ወጣት መምህራን ጋር በወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያካፈሉንን ከዚህ በታች በድምፅ ያገኛሉ።
ምንጭ፦ www.dw.de

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ