ሲዳማ ቡና ፕሪምየር ሊጉን በ5 ነጥብ ልዩነት በመምራት ላይ ነው

በትናንትናው እለት በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከነማን 1 ለ0 ሲያሸንፍ ሀዋሳ ከነማ ደግሞ ከሙገር ሲሚንቶ ኣቻለኣቻ ተለያይቷል።
ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ መከላከያን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች አርባምንጭ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ0 በሆነ ውጣት ሲጠናቀቅ፥ ደደቢት ዳሽን ቢራን በተመሳሳይ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። 
ፕሪሚየር ሊጉን ሲዳማ ቡና 11 ጨዋታዎች አድርጎ በ23 ነጥብ ሲመራ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ10 ጨዋታ 18 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ላይ ይገኛል እንዲሁም መከላከያ በ11 ጨዋታ በ16 ነጥብ  በሶስተኝነት ይከተላል።

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ