ዶ/ር ቤታና ሆጤሶ በሲዳማ ታሪክ ላይ ያደረጉት ወይይት Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps September 30, 2014 ዶ/ር ቤታና ሆጤሶ በሲዳማ ታሪክ ላይ ያደረጉት ወይይት፦ Dr Betana Hoxesso Sidama Liberation Front Vice Chair Person discuss about Sidama history Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች March 04, 2014 በተስፋዬ ንዋይ መነሻ የአገራችንን የአጭር ጊዜ ታሪክ በጥልቀት ለሚመለከት ታዛቢ እጅግ በጣም የሚያሰቅቅና አፍ የሚያሲዘን ጉዳይ የተወሰኑ የዕውቀት ገመዶች የጥፋት ብርሃን ማስተላለፊያ በመሆናቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ በተጨባጭ እውነት ላይ የተመሠረተ ሚዛናዊ ትንታኔ በበቂ ሁኔታ የተሰጠ አይመስለኝም፡፡ ይህ መሠረታዊ ሀቅ ንቅንቅ ወደማይል አለትነት የደረሰ ይመስላል፡፡ ይህን ችግር ከመሠረቱ የሚፈጥረው ደግሞ “የኢትዮጵያ ታሪክ” ተብሎ በጽሑፍም ሆነ በቃል የሚተረተረው ሐሳብ እውነታን መሠረት ያላደረገ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለፖለቲካ፣ ግብዓትና ዓላማ ተብሎ የቀረበ ወይም እየቀረበ ያለ መሆኑ ነው፡፡ ይህ መምታታት አገሪቷን አንድ አስማሚ የሆነ ታሪክ የሌላት የሚያስመስላት ብቻ ሳይሆን የግልን የፖለቲካ ዓላማ ማካሄጃ መድረክ እንዲሆን ዕድል ፈጥሯል፡፡ የአገራችን የታሪክ ሒደትና ውጤት ላይ በእውነት (Authentic) ላይ የተመሠረተ የታሪክ ዕድገት በአገሪቷ ተመዝግቦ ያለመኖሩ አንድ ችግር ሆኖ፣ እነዚህ በእውነት ላይ ያልተመሠረቱ ታሪኮችን ከእውነት በላይ አድርጎ በመውሰድ ምሁራዊ ትንታኔዎችን በእነሱ ላይ መስጠት ሌላው አበሳጭ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን እንድል ያደረገኝ በቅርቡ በገበያ ላይ ውሎ የተሰራጨውን “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚል ጥራዝ አንብቤ ከጨረስኩኝ በኋላ ነው፡፡ ይህ ጥራዝ የተጻፈው መስፍን ወልደማርያም በሚባሉ ግለሰብ (እኚህ ግለሰብ ፕሮፌሰር የሚል ማዕረግ የደረቡ ቢሆንም በመጽሐፉ ላይ ስላወለቁት እኔም ትቼዋለሁ) ሲሆን፣ በዚህ አጭር በማይባል ጥራዝ ጸሐፊው ያሉዋቸውን አስተሳሰቦችና ከአስተሳሰቦቹ ጀርባ ያሉትን መነሻዎች በሚገባን ቋንቋ አቅርበዋል፡፡ በዚህ ጥራዝ የታጨቁት ሐሳቦች ... Read more
የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት September 01, 2019 የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው... Read more
Sidama Buna Female Football Club April 03, 2014 Sidama Buna Female ( Football Club Photo @ http://sidamacoffeefc.com/ ) Read more
Comments
Post a Comment