የሲዳማ ቡና በሲዳሞ ቡናነት መጠራቱን ዛሬም ቀጥሏል
ከመቶ ኣመታት በላይ በኢትዮጵያ የነበረው የነፍጠኛው ስርዓት የህዝቦችን እና የኣከባቢዎቻቸውን መጠሪያ ሰሞች በመሰለኝ እና በደሳሌኝ በመቀየር የሚታወቅ ሲሆን፤ በዘፈቀደ የተለወጡት እነዚሁ መጠሪያ ስሞች በተለይ በዛሬው የህዝቦች ማንነት ላይ ተጽዕኖ በመፈጠር ላይ ናቸው።
ሲዳማ
የመጠረያ የስያሜ ሞድፊኬሽን ከተደረገባቸው
ህዝቦች መካከል ኣንዱ ነው። በሲዳማ የነበረው
የነፍጠኛው ስርዓት የሲዳማ ኣከባቢዎች መጠረያ
ሰሞችን ላይ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ መጠረያ ስም
ላይም ለውጦችን እስከማድረግ ደርሷል።
ለኣብነት
ያህል በሲዳማ ብሔር መጠረያ ስም ላይ ከተደረገው
ለውጥ በተጨማሪ በሲዳማ ከተሞች እና ወረዳዎች
ላይ መሰል ሞድፊኬሽን ተደርጓባቸዋል፦ሐዋሳን
ወደ ኣዋሳ፤ ሐርቤጎናን ወደ ኣርቤጎና፤
ሐሮሬሳን ወደ ኣሮሬሳ፤ ወዘተ ይገኙበታል።
እነዚህ
በዘፈቀደ የተደረጉት ለውጧች በብሔሩ ማንነት
ላይ ኣሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠራቸው በላይ ብሔሩ
እና ክልሉ በሁለት ስያሜ እንድጠራ የግድ
ብሎታል። ኣንድን ብሔር ወይም ህዝብ ያለኣግባብ
በሁለት ስም መጥራት ባለው ኣሉታዎ የፖለቲካ
እና ማህበራዊ እንድምታ ላይ በሌላ ጊዜ
የምመለስበት ሲሆን፤ ለዛሬ ግን ይህ በነፍጠኛው
የተተዎው የመጠረያ ስም ለውጥ ኣሻራ በሲዳማ
ምርቶች ላይ መንጸባረቅ መቀጠሉን በተመለከተ
ትንሽ ማለት እወዳለሁ።
እንደምታወቀው
በኣገሪቱ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ
በርካታ ኣከባቢዎች እና ህዝቦች በቀድሞው
መጠረያ ሰሞቻቸው መጠራት ጀምረዋል። ሲዳማም
ብሆን የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆኑ እውን ነው።
የመጠሪያ ሰሞችን ወደ ቀድሞ ስያሜዎቻቸው
የመመለሱ ጉዳይ በብሔር እና በኣከባቢዎች
ስያሜ ላይ ብቻ ሳይወሰን በብሔሩ እና በኣከባቢዎች
ምርቶች ላይም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።
ለምሳሌ
ያህል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሲዳማ ቡና ምርቶች
በቀድሞው መጠረያ ስሞቻቸውን እንድጠሩ የማድረግ
ዘመቻ በኣገረ ውስጥ እና ከኣገር ውጪ በሚኖሩ
ሲዳማውያን ከመደረጉ በላይ ምርቶቹን የማስተዋዎቅ
ስራም በመሰራት ላይ ነው። በዚህም የተነሳ
በኣገር ውስጥ የቡና ገበያ የሲዳማ ቡና ምርት
መጠረያ ከሲዳሞ ቡናነት ወደ ሲዳማ ቡና
የተለውጧል። ይህንን ለውጥ ተከትሎ እንደስታር
ባክስ የመሳሰሉ ታላላቅ የሲዳማ ቡና ገዥዎች
በምርቶቻቸው መጠረያ ላይ ለውጥ ያደረጉ ቢሆን፤
ጥቂት የማይባሉት ሌሎች የሲዳማ ቡና ገዥ
ኩባኒያዎች ግን የስያሜ ለውጥ ኣላደረጉም።
የሲዳማን
ቡና ምርት ከሚያከፋፍሉት ኩባኒያዎች በተጨማሪ
የሲዳማ ቡና ኣብቃይ ኣርሶ ኣደሮች ከምርቱ
ተጠቃሚ እንድሆኑ በመከራከራቸው የምታወቁት
የፌር ትሬድንግ ኣካላት የሲዳማን ምርቶች
በቀድሞ ስሞቻቸው መጥራታቸውን ቀጥለዋል።
በጀርመን፤ በእንግሊዥ፤ በፈረንሳይ እና
በጣሊያን የሚገኙት እነዚሁ የፌርትሬድንግ
ተቋማት የሲዳማን ቡና ምርት በቀድሞ ስሙ
ኣከባቢው ደግሞ በኣሁኑ ሲያሜው በማስተዋዎቅ
ላይ ናቸው። በመሆኑም የሲዳማ ምርቶች በትክክለኛው
መጠረያ ስሞቻቸው በኣገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን
በመላው ኣለም እንድታወቁ ለማድረግ የሚደረገው
እንቅስቃሴ የኣንድ ወቅት የፖለቲካ ወሬት
መደረግ የለበትም፤ ባይሆን ሁሉምን ባሳተፈ
መልኩ የቡና ምርቱን ከምገዙት ብሎም ምርቱን
ከሚያስተዋውቁት ኣካላት ጋር እጅለእጅ ተያይዞ
መካሄድ ይገቧዋል።
እነዚህ
በዘፈቀደ የተደረጉት ለውጧች በብሔሩ ማንነት
ላይ ኣሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠራቸው በላይ ብሔሩ
እና ክልሉ በሁለት ስያሜ እንድጠራ የግድ
ብሎታል። ኣንድን ብሔር ወይም ህዝብ ያለኣግባብ
በሁለት ስም መጥራት ባለው ኣሉታዎ የፖለቲካ
እና ማህበራዊ እንድምታ ላይ በሌላ ጊዜ
የምመለስበት ሲሆን፤ ለዛሬ ግን ይህ በነፍጠኛው
የተተዎው የመጠረያ ስም ለውጥ ኣሻራ በሲዳማ
ምርቶች ላይ መንጸባረቅ መቀጠሉን በተመለከተ
ትንሽ ማለት እወዳለሁ።
Comments
Post a Comment