የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አዘጋጅ አገር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ መስከረም 10/2007 የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን /ካፍ/ የ2019 ፣ የ2021 እና 2023 የአህጉሩን ዋንጫን ለማስተናገድ የተመረጡ አገሮች  ዛሬ ይፋ አደረገ።
በዚህ መሰረት 2019 የአፍሪካ ዋንጫ  ለማዘጋጀት ካሜሮን፣2021 ኮትዲቯር፣የ2023 ደግሞ ጊኒ አንዲያዘጋጁ ተመርጠዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት ዋንጫውን ለማስተናገድ ፍላጎት ያላቸው አገራት የማስተናገድ አቅም የሚያሳይ ፅሑፍና የ30 ደቂቃ ቪዲዮ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ለካፍ አመራሮች ቀርበዋል።
አልጄሪያ፣ ካሜሮን፣ ጊኒ፣ ኮትዲቯርና ዛምቢያ ዋንጫውን ለማዘጋጀት አቅም እንዳላቸው የሚያሳይ ፅሑፍ ያቀረቡ  አገራት ናቸው።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ