የሲዳማ ዞን መንግስት ከዞኑ ውጪ ነዋሪ በሆኑ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ኢሰብኣዊ ድርጊት ማስቆም ኣልቻለም፤ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ሮቤ ዞን የሀንጌቱ ወረዳ ኣስተዳደር የሲዳማ ብሔር ተወላጆችን እያፈናቀለ ነው
በቃጠሎ ከወደሙ ቤቶች መካከል |
በቃጠሎ ከወደሙ ቤቶች መካከል |
በቃጠሎ ከወደሙ ቤቶች መካከል |
- 46 ቤቶች ከእነ ንብረታቸው በቃጠሎ ወድሟል፤
- 400 የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ከኣከባቢው እንዲሰደዱ በመደረጋቸው ከ2 ወራት በላይ በጫካና በዱር እየተንገላቱ ነው
በኦሮሚያ
ክልል በባሌ
ሮቤ ዞን
በሀንጌቱ ወረዳ
ለኣመታት ከኣከባቢው ህዝብ ጋር
ተጋብቶና
ተዋልዶ በሰላም
የኖሩት
የሲዳማ
ብሔር ተወላጆች
በወረዳው ኣስተዳደር ቤት
ንብረታቸውን
ተቀምተው ከኣከባቢው እንድለቁ በመደረግ ላይ
ናቸው።
ሪፖርተራችን
ጥቻ ወራና ከሃዋሳ የላከልክ ዘጋባ እንደሚያመለክተው
ከሆነ፤ በወረዳው ኣስተዳዳር የተመራው የጸጥታ
ኃይል በኣንድ ቀን ብቻ46
ቤቶች
ከእነ ንብረታቸው በማቃጠል፣በ400
ሰዎች
ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈጸም ለዘመናት
ከኖሩበት አካባቢ እንድሰደዱ እና ከ2
ወራት
በላይ በጫካና በዱር እንድገላቱ ኣድርጓል።
ከ400
በላይ
በደል የደረሰባቸው የሲዳማ ተወላጆች በተወካዮቻቸው
የደረሰባቸውን ኢሰብኣዊ ድርጊት በመቃዎም
ብሎም በደሉ
እንዲቆምና በደል የፈፀሙ አካላት በህግ
እንዲጠየቁ ተፈናቃዮች ለፌዴራል ጉዳይ ሚንስቴር
አቤቱታ ቢያቀርቡም አቤቱታውን የተቀበለ
አካል ጉዳዩ እንዲጣራ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት
በስልክ ትዕዛዝ ሠትተናልና ሄዳችው የሚሰጣችሁን
መልስ ጠብቁ የምል
ምላሽ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
ሆኖም
እስከ ዛሬ
ድረሰ
ምንም መፍትሄ
ሳይሰጥ ተጨማሪ ነዋሪዎች ላይ ንብረት የማውደምና
የማፈናቀል እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ
ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የተፈናቃዮችን አቤቱታ
ተቀብሎ ለባሌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤትና
ለሀረና ቡሉቅ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
ጉዳዩ እንዲጣራ በቁጥር ሰመኮ/21/106/06
በቀን
09/11/2006
ዓ/ም
ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም፤
እስከ ኣሁን ድረሰ ምላሽ ካለመስጠታቸው
የተነሳ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ህጻናት
መጠለያ ኣጥተው በመሰቃየት ላይ ናቸው፡፡
በጉዳዩ
ላይ የሲዳማ ዞን መንግስት እስከ ኣሁን ድረሰ
ይህ ነው የምባል እርምጃ ኣለመውሰዱ ታውቋል።
Comments
Post a Comment