በሀዋሳ ሲካሄድ የሰነበተው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

በሀዋሳ ሲካሄድ የሰነበተው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

በ8 ክለቦች መካከል የተካሄደው የጥሎ-ማለፍ ዙር የተጠናቀቀው ባለፈው እሁድ ሰኔ 22 2006 ነው፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደደቢትን በመለያ ምት 5 ለ4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሻምፒዮንነት ክብሩን አረጋግጧል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ከነማን፣ ደደቢት ዳሸን ቢራን አሸንፈው ነው በፍጻሜው የተገናኙት፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ዓመትም የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ በሻህ በተገኙበት ለአሸናፊዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በውድድሩ ድንቅ የነበሩ ተጨዋቾችና ዳኞችም ተሸልመዋል፡፡
Source@http://www.ertagov.com/amharic/index.php/ethiopia-sport-news/ethiopia-football-news/item/4361-%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%8B%B5-%E1%89%A3%E1%8A%95%E1%8A%AD-%E1%8B%A8%E1%88%B4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8D%95%E1%88%AA%E1%88%9C%E1%8B%A8%E1%88%AD%E1%88%8A%E1%8C%8D-%E1%88%BB%E1%88%9D%E1%8D%92%E1%8B%AE%E1%8A%95-%E1%88%86%E1%8A%90

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ