ሁለት የሃዋሳ ከተማ ተጫዋቾችን የያዘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን ተሰማ


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ አስታወቁ።

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በዛሬው እለት ስለቡድኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።
አሰልጣኙ መግለጫ ከሰጡባቸው ዋነኛ ሀሳቦች መካከል ፥ የመረጧቸው 38 ተጨዋቾች የዝግጅት ሂደት ምን ይመስላል የሚለው ይጠቀሳል።
በተጨማሪም ዋነኛ አላማቸው በ2015 በሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ እንደሆነ በመግለፅ፥ አልጄሪያን ከመግጠማቸው በፊትም የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ቱርክ አቅንተው ለመጫወት እንደታሰበ አስረድተዋል።
አብዛኛውን ተጨዋቾች በደንብ ስለሚያውቋቸው ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል  ፀሀዬን እኔው እራሴ ምክትሎቼ አድርጌ መርጫቸዋለው ብለዋል በመግለጫቸው ላይ።
ከ20 አመት በታች የሚገኙ ተጨዋቾች የሚሳተፉበት  ክለቦች ሊግ በአገር ውስጥ ሊኖር እንደሚገባ እና  ተተኪዎችን ለማፍራት ከ14  ፣ 17 እና ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች ላይ መሰራት እንደሚኖርበትም ነው የገለፁት።
ዜናው የፋና ነው

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ