የሲዳማ ዞን የደኢህዴን ካድሬዎች የሲኣን/ መድረክን የሃዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሃዋሳ ከተማ ሰብሰባ ጠርተው እንደነበር ተሰማ

የሲዳማ ዞን የደኢህዴን ካድሬዎች የሲኣን/ መድረክን የሃዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሃዋሳ ከተማ ሰብሰባ ጠርተው እንደነበር ታውቋል።

በሃዋሳ ከተማ  በተካሄደው በዚህ ሰብሰባ ላይ በዞኑ ያለውን የክረምት የግብርና ኣካሄድ እና ኣያያዝን የተመለከተ እንድሁም የሲኣን ሰላማዊ ሰልፍ በዋና ኣጄንዳነት ተይዘው የዞኑ ኣመራሮች ተወያይቶበታል።

በመድረኩ ላይ ለሃዋሳው ሰላማዊ ሰልፍ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፤ በሲኣን ሰላማዊ ሰልፍ የነበረው የህዝብ ተሳትፎ ደኢህዴንን እንዳሳሰበውም በምገልጽ ሁኔታ የድርጅቱን የህዝብ ኣያያዙን ገምግሟል።

በሰብሰባውም ላይ የዞኑ ህዝብ የኢህኣዴግን መስመር ጥሩነት እንድቀበል በደንብ ማስተማር እንደምገባ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይ ሲኣን ለህዝቡ እንደማይጠቅም ኣስረግጠው ለህዝቡ ልነገረው እንደምገባ ተመክረዋል።

ሲኣን በሲዳማ ዞን ብቻ ሳይሆን በፌደራል ደረጃ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑን በማስረገጥ ላይ መሆኑ መገንዘባቸውን ያመለከቱ ሲሆን፤ የሲኣን ከሌሎች ኣገር ኣቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በማበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ እና መጠናከር የደኢህዴንን ህልውና ኣደጋ ላይ እንደምጥል በማመን ደህዴንን የማጠናከር ስራ ካድሬዎቹ እንድሰሩ ማሳሰባቸውን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘጋባ ያመለክታል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር