ለመሬት ኣስተዳደር ጠቀሜታ ኣለው የተባሌለት የሃዋሳ ከተማ ካርታ በቅርቡ ይጠናቀቃል

በአገሪቱ ለሚገኙ 23 ዋና ዋና ከተሞች የተዘጋጀው ካርታ በሚቀጥለው ወር ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአገሪቱ ለሚገኙ 23 ዋና ዋና ከተሞች እየተሰራ ያለው መሰረታዊ ካርታ በሚቀጥለው ወር መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን መሃመድ ዛሬ የኤጀንሲው 60ኛ አመት የምስረታ በዓል በተከበረበት ወቅት እንደተናገሩት ፥ ካርታ ከሚሰራላቸው 23 ከተሞች ውስጥ ባህርዳር ፣ መቀሌ ፣ አዳማ፣ አዋሳ ፣ ዲላ፣ ሆሳእና፣ ቢሾፍቱ፣ አሰላ፣ ሀረር ፣ ደሴና ጎንደር ይገኙበታል።
ከእነዚህ 23 ከተሞች በተጨማሪ የ68 አነስተኛ ከተሞች መሰረታዊ ካርታ በመሰራት ላይ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ይህ የካርታ ስራ ፕሮጀክት በ30 ሚሊዮን ብር ወጪ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የከተማ ልማት ቤቶች ኤጀንሲ ሚኒስቴር እንዲሁም በካርታ ስራ ኤጀንሲ የተሰራ ሲሆን ፥ ይህም በአገር አቅም የተሰራ የመጀመሪያ ፕሮጀክት ያደርገዋል።
የከተሞቹ ካርታ ሥራ ሲያልቅ የሌሎች እንደሚጀመር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ፥ በቀጣይ አመታት ሀገሪቱ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር እንደሚኖራት ተናግረዋል።
ካርታዎች በሳተላይት፣ በአየር ፎቶግራፍ እንዲሁም በምድር ቅየሳ የሚሰሩ ሲሆን የከተሞቹ ካርታ በአየር ፎቶግራፍ በከፍተኛ ጥራት የተሰሩ መሆናቸውም ተመልክቷል።
በተያያዘ የኤጀንሲው 60ኛ አመት ምስረታ በአል ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቪሽን፣ በሙዚየም ምረቃና በሌሎች ዝግጅቶች ''አስተማማኝ የጂኦ ስፓሽያን መረጃ ለዘላቂ ልማት'' በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
በዛሬው ዕለትም የተቋሙን የ60 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክር ሙዚየምና ኤግዝቤሽን በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሽዴ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር