ጥቂት የሲዳማ የእግር ኳስ ክለቦች ተጨዋቾችን የያዘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድን በቻን ውድድር ያለምንም ግብ ተሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የቻን አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፥ የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ላይ ከጋና አቻው ጋር አድርጎ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ዋሊያዎቹ ምንም ጎል ሳያስቆጥሩ በአራት የጎል እዳ ከምድቡ ተሰናብተዋል።
ጋናዎች የምድብ ሶስት መሪ ያደረጋቸውን ሶስት ነጥብ ያስመዘገቡት በ76ኛው ደቂቃ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ኩዋቢ አዱሴ ወደ ጎል በመቀየሩ ነው፡፡
በምድቡ ፥ ሊቢያ ኮንጎን በማሸነፍ  ጋናን ተከትላ ወደ ቀጣዩ ዙር የግማሽ ፍፃሜ ተቀላቅላለች፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

SIDAMA Micro-Finance Institution

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት