በሃዋሳ ከተማ መሃል ፒያሳ ላይ ከሴቶች ጋር በተያያዘ በቅርቡ ኣንድ የውጭ ዜጋ በሞቱን ተከትሎ በከተማዋ የጸጥታ ቁጥጥሩ ተጠናክሯል

በሃዋሳ ከተማ መሃል ፒያሳ ላይ ከሴቶች ጋር በተያያዘ በቅርቡ ኣንድ የውጭ ዜጋ በሞቱን ተከትሎ በከተማዋ የጸጥታ ቁጥጥሩ የተጠናከረ ሲሆን፤ በሙሉ ከተማዋ ፌደራል ፖሊስ በመኪኖች ታግዞ የጸጥታ ቁጥጥር ስራውን በመስራት ላይ ነው።
በከተማዋ የተሰማራው የጸጥታ ኣስከባር ኃይል የከተማዋን ጸጥታ ማስከበር የቻለ ሲሆን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራን ከተማዋን በመቃኘት ያላከልን መረጃ እንዳምያመለክተው የሃዋሳ ከተማ በኣሁኑ ጊዜ ሰላም የሰፈነባት ከተማ ሆናለች።
የሃዋሳ ከተማ የመዝናኛ ከተማነት ባለፈው የቱርዝም ኮንፎራንስግ ማዕከልም እየሆነች በመምጣት ላይ ያለች ከተማ ስለሆነ በጸጥታ ጉዳይ ላይ የምመለከተው ኣካል መስራት ይጠበቅበታል። በተለይ የጫምባባላ እና የቅዱስ ገብረኤል ንግስና በዓላትን የመሳሰሉ እጅግ በርካታ ሰዎች የምሳተፉበትን በዓላት የምታስተናግድ ከተማ መሆኗ በጸጥታ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት እንድሰጥባት የግድ ይላል። በዚህ ሳምንት ላይ የምከበረውን የታህሳሳ የቅዱስ ገብረኤል ንግስና በዓል ላይ ለመገኘት በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ከተማዋ የምመጣ በመሆኑ በጸጥታ ኣጠባበቅ ላይ ትኩረት መሰጠት ኣለበት።
የከተማዋን ሰላም እና ጸጥታ በዘላቂነት ለማስከበር መንግስት ኣሁን እያደረጋ እንዳለው ችግሮች ከተከሰቱ በኃላ ላይ ብቻ የጸጥታ ኃይልን ከማሰማራት ዘላቂ የሆነ ጸጥታ የማስከበር ስራዎችን ብስራ መልካም ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር