በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ሲዳማውያን በኢኮኖሚው ዘርፍ ብቁ ተወዳደር መሆን ኣልቻሉም፤በንግድ ስራ ከሌላው ብሄር እኩል ለመስራት ብዙ የልምድ ማነስ ይታይባቸዋል


እንደምታወቀው ኣብዘኛውን ቁጥር የምይዘው የሲዳማ ህዝብ የምኖረው በገጠር ነው። ሲዳማ ወደ ከተማ መግባት የጀመረው የኢህኣዴግ መግባትን ከተትሎ ነው። በወቅቱ የሲዳማውያን በገዛ ከተሞቻቸው ውስጥ ገብተው መኖር እንዲጀምሩ በምል የዞኑ መንግስት ብዙ እድሎችን በመፍጠር የህዝቡን ወደ ከተማ መግባት እና ወደ ከተሜነት መለወጥን ኣበረታቷል፤ ምንም እንኳን እንደታለመለት ሳይሆን ወደ ሃዋሳ እና ወደሌሎች የሲዳማ ከተሞች የገባው የገጠሩ ህዝብ በመንግስት የተሰጣቸውን መሬት ለሌላ ብሄር ተወላጅ ባለሃብቶች በመሸጥ እጅ ነካሽ ብሆኑም።

ለኣብነት ያህል ከዛሬ ኣስር እና ኣስራም ኣምስት ኣመት ጀምሮ በተለይ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ የሲዳማውያን በኢኮኖሚው የበላይነት እንዲኖራቸው ሲባል ለንግድ የምሆኑ ግንባር የሆኑ ቦታዎች በዞኑ መንግስት እና በከተማዋ ኣስተዳደር ለበርካታ ሲዳማውያን የተሰጠ ሲሆን፤ የተሰጣቸው መሬት ላይ የንግድ ቤቶችን በመገንባት የእድሉ ተጠቃሚ ከመሆን ኣብዛኛዎቹ የተሰጣቸውን መሬት ከላይ እንዳነሳሁት ለሌላ ብሄር ተወላጂ ባላሃብቶች በመሸጥ ሌሎቹን ጠቅመዋል ሲጠቅሙም ይታያል። በከተማዋ ግንባር ቀደም የሆኑ ቦታዎች ወይም በኣሁኑ ጊዜ ትላልቅ የንግድ ቤቶች ተሰርቶባቸው ብዙ ገንዝብ በማስገባት ላይ ያሉ ቦታዎች የዛሬ ኣምስት እስከ ኣስር ኣመታት በፊት ባለቤቶቻቸው እኔማናቸው ከተባለ መልሱ መቶበመቶ ሲዳማዎች እንደሆኑ ብዙ ሳይደከም የደረስበታል።

በርግጥ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ የሲዳማ ባለሃብት የለም ማለት ኣይደለም። በከተማዋ ውስጥ በመገንባት ላይ ከምገኙ ህንጻዎች ውስጥ በሲዳማ ባላሃብቶ በመገንባት ላይ ያሉ በርካታ ናቸው፤ ነገር ግን እንደከተማዋ ባላቤት ፤ ካለው የኢኮኖሚ ጡንቻ እና የዞኑ እና የከተማ ኣስተዳደር ከፈጠረላቸውም ምቺ የስራ እድል ኣንጻር ኣልተጠቀሙም። እንደ ጥቻ ወራና ዘጋባ ከሆነ ሲዳማውያን በሃዋሳ ከተማ ውስጥ በተለይ በንግድ ስራ ከሌላው ብሄር እኩል ለመስራት ብዙ የልምድ ማነስ ይታይባቸዋል። የተለያዩ የንግድ ስራ ለመስራት ተብሎ በሲዳማውያን የተገነቡ ህንጻዎች ለሌሎች ስዎች በክራይ ተሰጥተው ሌሎች ሰዎች ይነግዱበታል። የዞኑ መንግስት የሲዳማን ወጣቶች በንግድ እና በገንዘብ ኣያያዝ ላይ ግንዛቤ ልፈጥሩ የሚያስሉ ስራዎችን መስራት ካልቻለ ሲዳማውያን በሃዋሳ ከተማ በንግድ ተወዳዳር የመሆን እድል የጠበበ ነው።

በሃዋሳ ከተማው ሲዳማውያን የምሳተፉባቸው የንግድ ስራዎችም የተወሰኑ ይመስላሉ ለኣብነት ያህል፤በገዛ ከተማቸው ከሌላው እኩል ባላቸው ሃብት ተጠቃሚ ልያደርጋቸው የምችል ስራዎችን መስራት ሲችሉ የምሰሩት ግን በኣብዛኛው ከቡና ንግድ ጋር የተያያዘ ስራ ብቻ ነው። እንደምታወቀው በኢኮኖሚው ዘርፍ ዘርፌ ብዙ የሆነ መሰረት ያለው ኢኮኖሚ መገንባት ካልተቻለ በቡና ብቻ የተሞለኮዝ ኢኮኖሚ ዘንድሮ እንዳየነው ኣይነት የቡና ዋና መውረድ ሲገጥመው ወደ ቀውስ መግባቱ ኣይቀረ ነው። ለዚህም ሲዳማውያን የኢኮኖሚ መሰረታቸውን በበርካታ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ መጣል የግድ ይላቸዋል።

እንደ ጥቻ ወራና ኣባባል ከሆነ በሃዋሳ ከተማው ውስጥ የሆቴል፤ሬስቷራንት፤ካፌ፤ ሱፐርማርኬት እና የመሳሰሉት የንግድ ስራዎች ሲዳማዎች የማይሳተፉባቸው ከመሆናቸው የተነሳ ለሌላው ብሄር ብቻ የተተው እስኪመሰል ደርሰዋል። ይህንን ማለት ሃዋሳን በሚያክል በካፊቴርያ ቤቶች ብዛት በምታወቅ ከተማ ውስጥ በሲዳማውያን ባሌበትነት የምተዳደር እንደነ ሎግታ ካፌን ኣይነቶቹን የተወሰኑ ካፌዎች ማየት የምገርም ነው ማለታች ነው።

ለማንኛውን በመላው ኢትዮጵያ፦በትግራይ፤ ኣማራ፤ ኦሮሚያ እና በሌሎች መሰል ኣካባቢዎች ያሉ የየኣካባቢው መንግስታት ለህዝቦቻቸው እንደምያደርጉት ሁሉ የሲዳማ ዞን መንግስት በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ያለውን የሲዳማውያንን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመቃኘት በንግድ እና በሌሎች ገቢ ማስገኛ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ያሉባቸውን ችግሮ በማጥናት ችግሮቹን የመቅረፊ እና በኢኮኖሚ የባላይነት የምጎናጸፉበትን መንገድ ቢያመቻች መልካም ነው።
መልካም ጊዜ!

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር