ሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከነማ ሲያሽንፍ ሲዳማ ቡና ሽንፈትን ኣስተናግዷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትናንት እና ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።
በዛሬው ዕለት ከተካሄዱ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የመከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወጥቷል።
ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ላይ ወላይታ ዲቻ ከ ሃረር ቢራ ያለምንም ግብ 0  ለ0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
እዛው ሃዋሳ ላይ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ሃዋሳ ከነማ ዳሽን ቢራን 2ለ 0 ሲያሸንፍ ፤ አዲስ አበባ ላይ ንግድ ባንክ ሙገር ሲሚንቶን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ምሽት ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ5 ጨዋታ 15 ነጥብ በመያዝ ሲመራ ፥ እኩል 7 ጨዋታ ያደረጉት መከላከያ እና ንግድ ባንክ በ14 ነጥብ ይከተላሉ።
የአምናው አሸናፊ ደደቢት በ4 ጨዋታዎች 10 ነጥብ ይዞ ይከተላል። 

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ