በወላይታ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በኣከባቢው ነዋሪዎች የምደርስባቸውን ግፍ እና ስቆቃ መቋቋም ስላቃታቸው የሲዳማ ዞን እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር ጠልቃ እንድገባ እየተማጸኑ ነው

በወላይታ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በኣከባቢው ነዋሪዎች የምደርስባቸውን ግፍ እና ስቆቃ መቋቋም ስላቃታቸው የሲዳማ ዞን እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር ጠልቃ እንድገባ እየተማጸኑ ነው።

በካላ ማቲዎስ የቴ በተባሉ የተጎጂዎች ተወካይ በኩል በቪድዮ  ተደግፎ  በተላለፈው መልዕክት ላይ እንደተገለጸው፤ የኣካባቢው ነዋሪዎች
በሲዳማ ተወላጆች ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስ ኣልፈው ኣከባቢውን በኣስቸኳይ ለቀው ካልወጡ በንብረታቸው እና በእነርሱም ላይ ጥቃት እንደምፈጽሙ በማስፈራራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። 

በኣገሪቱ ብሎም በክልሉ ዜጎች እንደልባቸው በየትኛውም ኣካባቢ የመዘዋወር እና የመኖር ብሎም ንብረት የማፍራት መብት በህገ መንግስት
ተደንግጎ  እያለ ይህን መሰል የሰብኣዊ መብት ጥቃት በሲዳማ ተወላጆች ላይ መድረሱ የኣገሪቱን ህገ መንግስት ጭምር የጣስ ኣካሄድ ነው ።

በቪድዮ  ተደግፎ  የቀረበውን ይህንን  መልዕክት ከላይ ይመልከቱ

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ