አምስተኛው የከተሞች ሳምንት በባህር ዳር ይከበራል፤ ከሲዳማ ከተሞች ምን ይጠበቃል?

የሲዳማ ከተሞች ከሆኑት ኣለታ ወንዶ፤ ዳሌ-ይርጋኣለም እና ከሃዋሳ በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ የከተሞች ውድድይ ምን ይጠበቃል? ዝግጅታቸው ምን ይመስላል? መረጃ ያላችሁ ሰዎች ተጋሩን።
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው የከተሞች ሳምንት  በ2006 ዓ.ም  ከህዳር 11 አሰከ 17 በባህር ዳር ከተማ ሊከበር ነው።
በአሉም  "ከተሞቻችን  የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማእከላት በመሆን የመለስን ሌጋሲ ያስቀጥላሉ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
ለበአሉ አከባበር ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴርና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር  ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
 ለዚሁም በአሉ የሚመራበትን መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፤ ዝግጅቱን የሚያስተባብሩ የተለያዩ አደረጃጀቶችም በፌደራል፣ በክልሉ መንግስትና  በከተማዋ አስተዳደር ደረጃ ተቋቁሟል።
 የበአሉ አላማም በከተሞች መካከለ ውድድርን መፍጠርና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን በማበረታታት ለሌሎች ከተሞች አርአያ አንዲሆኑ ማድረግ ነው።
 ከ17 ሺ በላይ ህዝቦች ያሉዋቸው ከ150 በላይ ከተሞች በባአሉ ይሳተፋሉም ተብሎ ይጠበቃል።
 አራተኛው የከተሞች ሳምንት በያዝነው አመት 132 ከተሞችን በማሳተፍ  በአዳማ ከተማ መከበሩ ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት