የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅ ተግባራዊ ያደረጉ ከ98 ሺህ የሚበልጡ ሞዴል ቤተሰቦች ተመረቁ


ሐዋሳ ነሐሴ 20/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው በጀት አመት በአንድ ለአምስት ትስስር ሰልጥነው የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ያደረጉ ከ98 ሺህ የሚበልጡ ሞዴል ቤተሰቦች መመረቃቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ የሥራ ሂደት ባለሙያ አቶ አበበ በካ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በዞኑ የጤና ልማት ሠራዊት ግንባታን በማጠናከር የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራምን ስኬታማ ለማድረግ የአንድ ለአምስት ትስስር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዞኑ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ በሽታን የመከላከል የጤና ፖሊሲ ውጤታማ እንዲሆን በተፈጠረው የአንድ ለአምስት ትስስርት በተጠናቀቀው በጀት አመት ስልጠና ወስደው የጤና ኤክስቴሽን ተግባራዊ ያደረጉ ሞዴል ቤተሰቦች መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ከ30 ሺህ በላይ ቤተሰቦች አሁንም ስልጠና እየወሰዱ መሆኑንና ከዚህ በፊት የተመረቁትን ጨምሮ ሞዴል የጤና ቤተሰቦች ቁጥር በዞኑ 603 ሺህ 367 መድረስ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡ ከሁለት አመት በፊት በዞኑ ከተሞች በተጀመረው የከተማ ጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም የሰለጠኑ 2 ሺህ 337 የከተማ ሞዴል የጤና ቤተሰቦች መመረቃቸውን አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡ የተመረቁት የጤና ሞዴል ቤተሰቦች በግልና አካባቢ ንጽህና፣በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣በመፀዳጃ ቤት ንጽሕና አያያዝ፣በገጠር መፀዳጃ ቤት በመገንባት ተጠቃሚና የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ የቻሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት