በተያያዘ ዜናም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን 1ኛ አመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ የሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ነዋሪዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጀጐ አገኘው በችግኝ ተከላው ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በተለይ በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ላይ በኢትዮጵያም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ራዕይ ነበራቸው፡፡
ይህንንም ራዕያቸውን ለማሳካት በወረዳው 14 ፓርኮች ተለይተው በ127 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል ከታቀዱት 32 ሺህ ችግኞች ግማሽ ያህሉ ተከላ ተከናውኗል ብለዋል፡፡
ቀሪ ችግኞችን የመትከሉ ሁኔታም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው  አቶ ጀጐ የገለፁት፡፡
በችግኝ ተከላው ያነጋግርናቸው የወረዳው ነዋሪዎችም ችግኞችን በመንከባከብ ረገድም ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ የአረንጓዴ ልማቱን እናሳካለን ማለታቸውን የዘገበው በኃይሉ ጌታቸው ነው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/16NehTextN305.html

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት