የአካባቢ ምርጫ በኢትዮጵያ


የአዲስ አበባ ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ መራጮች ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ዉለዋል። ዛሪ የጀመረዉ የኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የአካባቢ የአዲስ አበባ እና የድሪደዋ ከተሞች አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ በቀጣይ ማጠቃለያ ልክ የዛሪ ሳምንት የሚከናወን መሆኑ ተነግሮአል።
በዛሪዉ የመጀመርያ ፈረቃ ምርጫ በአዲስ አበባ የነበረዉን ሂደት የተከታተለዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሄር፤ እንዲሁም የሱሉልታን አካባቢ የምርጫ ሂደት የተከታተለዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሃ/ጊዮርጊስ ዘገባ አድርሰዉልናል።
በሌላ በኩል ዛሪ በተካሄደዉ የክፍለ ከተማና የከተማ አስተዳደር ምርጫ ከሰላሳ አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅን ለመስጠት መመዝገቡን የሀገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ። ዛሪ ከቀትር በኃላ ዘጠኝ ሰዓት ግድም ላይ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱፊን በስልክ አግኝተን ስለምርጫዉ አጠቃላይ ሂደት ጠይቀናቸዉ ነበር።
አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር