ኢትዮጵያን ከኬኒያ የሚያገናኘው የአዲስ አበባ - ሀዋሳ - ሞያሌ መንገድ ግንባታ አካል የሆነ የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ፡፡


ኢትዮጵያን ከኬኒያ የሚያገናኘው የአዲስ አበባ - ሀዋሳ - ሞያሌ መንገድ ግንባታ አካል የሆነ የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ፡፡
በአዲሱ ፕሮጀክት ስምምነት መሰረት መንገዱ እያንዳንዳቸው 7 ሜትር የሚሰፉ ሁለት መተላለፊያዎች ይኖሩታል፡፡በተጨማሪም የመንገዱ ቀኝና ግራ ጠርዞች 1 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ይኖራቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወ/ገብርዔል መንገዱን ከሚገነቡት ሁለት የህንድ ተቋራጮች ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ባለስልጣኑ አሁንም ብቃት ያላቸውን ሌሎች ተቋራጮች በግንባታው ላይ ለማሳተፍ ጥረት እያደረገ መሆኑ ገልጿል፡፡
የፕሮጀክቱ ስምምነት ሁለት ቢሊዮን ብር ያህል ሲሆን 85 ከመቶ ያህል ወጪ ከአፍሪካ ልማትባንክ በተገኘ ብድር የሚሸፈን ነው፡፡
የመንገዱ ግንባታ በ3 ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ