ሀዋሳ ከነማ ሀረር ቢራን 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን በ25 ነጥብ ያዘ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከነማ ሀረር ቢራን 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን በ25 ነጥብ አጠናክሯል፡፡
ዛሬ መጋቢት 19/2005 ዓ.ም ከተካሄዱት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከነማ ሀረር ቢራን 1 ለ 0፣ መብራት ሀይል ደደቢትን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
ለሀዋሳ ከነማ የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው አንዷለም ንጉሴ/አቤጋ/ከእረፍት መልስ ነው፡፡
አዲስ አበባ ላይ ደደቢት እና መብራት ሀይል ባካሄዱት ጨዋታ ደደቢት በጌታነህ ከበደ አማካኝነት ባስቆጠራት ግብ ቢመራም በረከት እና ሳሚዔል ባስቆጠሯቸው ጎሎች መብራት ሀይል አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ገ/ማሪያምና ያሬድ ዝናቡ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
አዳማ ላይ አዳማ ከነማ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በአወዛጋቢ ክስተት ተቋርጧል፡፡
የአዳማውን ጨዋታ የመሩት ዳኛ በአንድ ክስተት 3 የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፋቸው ለጨወታው መቋረጥ ምክንያት ሆኗል፡፡
ፕሪሚየር ሊጉን ሀዋሳ ከነማ በ25 ነጥብ ደደቢት በ24ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ኢትዮያ ቡና በ22 ነጥብ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡
ምንጭ ኢቲቪ

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ