በሴቶች የፕሪምየር ሊግ ውድድር ሲዳማ ቡና ሩብ ፍፃሜ ገባ


PDFPrintE-mail
ሰኞ, 24 ታህሳስ 2012 11:05

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢትና ሲዳማ ቡና ከየምድባቸው በበላይነት አጠናቀዋል። የምስራቅ ዞን ምድብ አሁንም መጨረሻው አልታወቀም። 
ህዳር 29/2005 የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሴቶች ውድድር ሶስተኛ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ ማለትም ታህሳስ 13 እና 14/2005 ቀጥሎ ተካሂዷል። በቅዳሜው ጨዋታ የማእከላዊ ዞን ምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። በዚህም ደደቢት ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በመርታት ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ 1ኛ ሆኖ ያጠናቀቀበትን ውጤት ይዞ ወጥቷል።
መብራት ሃይልን 3 ለ 1 የረታው ኢትዮጵያ መድህንም በ6 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ሩበ ፍፃሜ መግባቱን አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቡናና መብራት ሃይል ከምድቡ ሳያልፉ ቀርተዋል።
ቀሪ 4 ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ ተከናውነዋል። በማዕከላዊ ዞን የምድብ ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታድየም ሲከናወኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ላይ ከደርዘን በላይ ግቦችን አስቆጥሯል።
ንግድ ባንክ 14 ለ 0 የረታበት ጨዋታ በዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል። ከ14ቱ ግቦች ሽታዬ ሲሳይ በግሏ 7ቱን ግቦች ከመረብ ስታገናኝ፣ ረሂማ ዘርጋ 5ቱን በስሟ አስመዝግባለች። የሽታዬ ሲሳይ እህት የሆነችው ብዙነሽ ሲሳይ ደግሞ ቀሪዎቹን ሁለት ግቦች አስቆጥራለች።
በዚህም መሠረት ሶስቱንም ጨዋታዎች በአሸናፊነት የተወጣው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምድቡን በበላይነት አጠናቋል።
በዚሁ ምድብ እኩል የማለፍ እድል ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት መከላከያና የቅ/ጊዮርጊስ 1 ለ 1 ተለያይተዋል። ሁለቱም 4 ነጥቦችን በመያዝ መከላከያ የተሻለ የግብ ክፍያ ስላለው ንግድ ባንክን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜ የተቀላቀለ ክለብ ሆኗል። ቅ/ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ዉሃ ስራዎች ከምድቡ ሳያልፉ ቀርተዋል።
በደቡብ ዞን ሀዋሳ ከነማ አርባምንጭ ከነማን 4 ለ 1 በመርታት 3 ነጥብ ይዞ ሲዳማ ቡናን በመከተል ግማሽ ፍፃሜ ገብቷል።
በምስራቅ ዞን ድሬደዋ ከነማ ሀረር ቢራን 8 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። ከዚህ በፊት አዳማ ከነማ ድሬደዋ ከነማን 2 ለ 1 በመርታቱ ድሬደዋ ከነማና አዳማ ከነማ እኩል 3 ነጥብ ይዘዋል። አዳማ ከነማ ገና ከሀረር ቢራ አልተጫወተም።
በዚሁ ምድብ የተደለደለው ሙገር ሲሚንቶ በውድድሩ ይካፈል አይካፈል አሁንም የታወቀ ነገር የለም።በዚህ ምክንያት የምድቡ አላፊዎች እነማን እንደሆኑ እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም።
http://www.ertagov.com/ertasport/erta-tv-news-football-addis-ababa-ethiopia/39-amharic-news-catagory-of-sport-football-erta-tv-addis-ababa-ethiopia/1388-2012-12-24-11-06-53.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር