የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ 35 ኣምስተኛውን የምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ኣከበረ፤ ኣዳዲስ የድርጅት ኣመራር መርጧል

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ 35 ኣምስተኛውን የምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ኣከበረ፤ ኣዳዲስ የድርጅት ኣመራር መርጧል

በዛሬው እለት በሃዋሳ ከተማ በዳግም ጂሚናዥዬም በተካሄደው የምስረታ  ሰነስርኣት ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ  35 ኣመት የምስረታ በኣል በተለያዩ  ዝግጅቶች ኣክብሯል።

በርካታ የድርጅቱ ደጋፊዎች በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስነስርኣት ላይ ለሲዳማ ህዝብ ነጻነት ለተሰው ሰማዕታት የህልና ጸሎት የተደረገ  ሲሆን ድርጅቱን በቀጣይነት የምመሩ ኣመራሮች ተመርጠዋል።

በኣጠቃላይ 15 ኣባላት ያሉት በኣብዛኛው ወጣቶችን የሆነና የዩኒቨርሲቲ ተማርዎችን ያቀፈ የድርጅት ኣመራር የተመረጠ ሲሆን ኣንጋፋ የሲዳማ ታጋዮችን በኣመራርነት ተካተዋል።

በኣመራርነት ከተመረጡት መካከል ካላ ዋቃዮ፤ ዶክተር ኣለማዬሁ፤ እና ካላ ካሳ ኣዲሶ  ይገኙበታል።

ክቡራን ኣንባቢያን  ዝርዝር ዜናውን እንደደረሰን እናቀርባለን

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ