የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለአቶ መለስ መታሰቢያነት እንዲውል ተወሰነ


የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያነት በማዋል እንዲከበር መወሰኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ እንደ ዋልታ ዘገባ፣ ከመጪው ኅዳር ወር መጀመርያ አንስቶ ለአንድ ወር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በየደረጃው የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል መታሰቢያነቱ በሞት ለተለዩት አቶ መለስ እንዲሆን የወሰነው ምክር ቤቱ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ይህን የወሰነው ባለራዕዩ መሪ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች እኩልነት አብዛኛውን ዕድሜያቸውን በፅናት የታገሉለት ዓላማ ስለነበር ነው መባሉን ዘገባው አስረድቷል፡፡ የዘንድሮ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን “ብዙም አንድም ሆነን የታላቁ መሪ ራዕይ በሕገ መንግሥታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተጠቁሞ፣ ከመጪው ወር መጀመርያ ጀምሮ በአገሪቱ ሁሉም ቀበሌዎች ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ በብሔራዊ ደረጃ ኅዳር 29 ቀን በባህር ዳር ከተማ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ