በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በመኸር ግብርና ሥራ 13 ሺህ 6 መቶ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ


የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታዲዮስ ነጤ እንደገለፁት የአምስት ዓመቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽ እቅድን ከግብ ለማድረስ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ባለፈው በልግ ወቅት 16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው ውስጥ 1 ሚሊዮን 6 መቶ ኩንታል መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡

የግብርና ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ 37 ሺህ 7 መቶ ኩንታል ዳኘና ዩሪያ ለአርሶ አደሩ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ  ማሰራጨት መቻሉን አቶ ታድዮስ አስረድተዋል፡፡
ሀገራችንን ከድህነት ለማውጣት የተያዙ ውጥኖችን ከግብ ለማድረስ አርሶ አደሩ፣ የግብርና ባለሙያው፣ የልማት ሠራተኛውና የአመራር አካላቱ በቁጭትና ወኔ በመነሳሳት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ አክሊሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/24MesTextN205.html

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ