ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ ከቡና የወጪ ንግድ 1.18 ቢሊዬን ዶላር ለማግኘት አቅዳለች


ኢትዮጵያ በ2005 በጀት አመት ከቡና የወጪ ንግድ 1.18 ቢሊዬን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ማቀዷን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድ ሚኒሰትሩ አቶ ከበደ ጫኔ በ2004 በጀት አመት የ832 ሚሊዬን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸው በበጀት አመቱ የታዩ ድክመቶችን በማረም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፈው በጀት ዓመት ለተገኘው ገቢ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ላኪዎችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ሰጥቷል፡፡

በዕለቱ ተሸላሚ የሆኑ ላኪዎችም ከመንግስት ጋር የበለጠ ተቀራርቦ በመስራት አገሪቱ ከዘርፉ ለማግኘት ያቀደችውን የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የቡና የወጪ ንግድን የ2004 አፈጻጻምና የ2005 እቅድ መሰረት ያደረገ ውይይት በግዮን ሆቴል ተካሂዷል፡፡
ETV

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ