በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባኤ ሊካሄድ ነው ለውጭ ገበያ ከሚቀርበው ቡና 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደሚገኝ ይጠበቃል


አዲስ አበባ ጥቅምት 16/2005 በቡና ንግድ ዘርፍ መላው ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖትርስ አሶሴሽን አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለዓለም አቀፉ ገበያ ከምታቀርበው የቡና ምርት 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደምታገኝ ይጠበቃል፡፡
የአሶስዬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አቶ ጌታቸው አድማሱ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ጉባኤው የቡና ምርቶች መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን ገጽታን ከመገንባት ባሻገር የተለያዩ ምርቶቿን ለዓለም አቀፉ ገበያ ለማስተዋወቅ የሚረዳ ነው፡፡
አሶስዬሽኑ ጉባኤውን በሚቀጥለው ሳምንት በአዲስ አበባ ሒልተን ለማካሄድ ከንግድ ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንና በአሁኑ ወቅትም አስፈላጊውን ቅድም ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀና በሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ የቡና ጉባኤም 250 ሰዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡
እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ ከአገር ውስጥ በቡና ንግድ የተሰማሩ ላኪዎችና አቅራቢዎች ድርጅቶች፣ የሕብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖችና የክልል ግብርና ቢሮ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ተጠሪዎችና የገንዘብ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡
በተጨማሪም ከውጭ ዓለም ዓቀፍ የቡና ገዢዎች፣ ቆይና ቸርቻሪዎች የጉባኤው እድምተኞች ይሆናሉ፡፡
በጉባኤውም በተለይ በቀጣዩ አውሮፓውያን ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ምርት የውጭ ገበያ አቅርቦት በሚያድግበት እንዲሁም አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኝው የውጭ ምንዛሪ ገቢም በዚያው ልክ የሚጨምርበት ሁኔታ በመምከር አዎታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
በዓለም ዓቀፉ ገበያ የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ አቅርቦት አሁን ካለበት መጠን በ25 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡ ከ200 ሺህ ቶን በላይ እንደሚሆንም ከወዲሁ ተተንብዩዋል፡፡
ኢትዮጵያ ይህን ያህል የቡና ምርት ለዓለም አቀፋ ገበያ በማቅረብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደሚያስገኝላትም ገልጸዋል፡፡
ይህ ገቢ በአገሪቱ አዲስ ሪከርድ መሆኑንና በታሪኳም ሰባት አሃዝ ያለው ገቢ ከነጠላ ሸቀጥ ሽያጭ በወጪ ንግድ ዘርፍ ስታገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=2976&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር