የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ከተሰማ ጀምሮ መግለጫ ከሰጡት መካከል በሲዳማ ዞን ስር የሚገኙ የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ፣ መንገዶችና ትራንስፖርት መምሪያ፣ የዳሌ ወረዳ አስተዳደር በሃዋሳ ከተማ የዳካ ቀበሌ ታዳጊ ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ እንዲሁም የሀዲያ ዞን ንግድና ኢንዲስትሪ ልማት መምሪያ ይገኙበታል፡፡


ባለራዕይና የዘመናችን ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ሁሉአቀፍ እውቀትና የመምራት ብቃት ያላቸው በሳል መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡
በተመሳሳይም በይርጋዓለም ከተማ የሠላም አንድነት አረጋዊያን ማህበር የተስፋ ራዕይ አውራጅና ጫኝ ማህበር፣ ራይስ ኢንጀነሪንግ ኒያላ ሞተርስ፣ ሲዳማ ቡና አቅራቢዎች ማህበር፣ ፖራዳይስ ሆቴል፣ ይርጋዓለም ኮንስትራክሽንና  ኦሲስ ሆቴል ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች፣ ሃላፊዎቹና ባለቤቶቹ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

መሪያችን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ አሌኝታ  የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ ያሉት መግለጫ  ሰጪዎቹ በእሳቸው የተጀመሩትን እቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ስራቸውን ከመቃብር በላይ ሲታወሱ እንዲኖሩ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በተለይም ይህን የሰነቁትን ዓላማ ወጣቱ ትውልድ በደንብ ተገንዝቦት በጋራ የመረባረቡን ሃላፊነት እንዲወጣ አደራቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤተሰቦቻቸውን መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ