ሃዋሳ የቱሪስት ከተማ ልትመሰርት ነው



አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 24፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃዋሳ ሌላ የቱሪስት ከተማ ለመመስረት በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

ከተማው የሃዋሳ ሃይቅን ተሻግሮ በሚገኝ ባዶ ቦታ ላይ ነው የሚመሰረተው።

በዚህ ከተማ ላይ ለቱሪስት ምቹ የሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ የመዝናኛ ሎጆችና ሪዞርቶች እንደሚገነቡ ነው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ የተናገሩት።

የቱሪስት ከተማው ሃዋሳን መርጠው ለመመልከት የሚመጡ የውጭና የሃገር ውስጥ ጉብኝዎችን ቁጥር በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም አመልክተዋል ።

የሚመሰረተውን ከተማና ነባሩን ከተማ ለማገናኘት የሚያስችል የትራንስፖርት ስርዓትም እንደሚዘረጋ ተመልክቷል ።

እንደ ባልደረባችን  ታደሰ ብዙዓለም ዘገባ የቱሪስት  ከተማዋን ምስረታ  ለመጀመር የሚያስችል ጥናት  ተጠናቆ  ትግበራን  እየተጠባበቀ ይገኛል ።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ