የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ከአለታ ወንዶ አካባቢ ደንበኞቹ ከ2 ነጥብ 7ሚሊዮን ብር በላይ በቁጠባ ሰበሳበ፤ተቋሙ ለደንበኞቹ ከሰጠው የብድር አገልግሎት ከ520 ሚሊዮን ብር በላይ በቁጠባ ሰበሰበ


አዋሳ ነሐሴ 02/2004 የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በደቡብ ክልል የብድር አገልግሎት ከሰጣቸው ደንበኞች በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ520 ሚሊዮን በር በላይ በቁጠባ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
በዚሁ የስራ ዘመን ከ767 ነጥብ 8ሚሊዮን ብር በላይ በብድር ማሰራጨቱም ተመልክቷል፡፡
የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሰሎሞን ገለቱ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ገንዘቡ የተሰበሰበዉ የብድር ተጠቃሚ ከሆኑት ከ300 ሺህ ከሚበልጡ ደንበኞች ላይ ነው ።
በክልሉ የተለያዩ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙት ደንበኞች በማህበር ተደራጅተውና በግል በተሰጣቸው የብድር ገንዘብ ልዩ ልዩ የስራ መስኮች ፈጥረው በመሰማራት ካገኙት ትርፍ ላይ መቆጠባቸውን አስረድተዋል፡፡
ተቋሙ በበጀት አመቱ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ ከ91 ሺህ በላይ አዲስና ነባር ደንበኞች ከ767 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱንም ሃላፊው አመልክተዋል፡፡
የተሰራጨው የብድር ገንዘብ ከ2003 የበጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በ51 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው የተሰራጨውም ገንዘቡ በግል እስከ 5ሺህ ብር በማህበር ደግሞ እስከ 100ሺህ ብርየሚደርስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብድሩ ተጠቃሚ ደንበኞች በወሰዱት የብድር ገንዘብ በከብት ማደለብ ፣ በዶሮ እርባታ፣ በእርሻ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ዘርፎች መሰማራታቸዉን አስታዉቀዋል ።
የተቋሙ ዲላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው በዳሶ በበኩላቸው በጌዴኦ በቡርጂና በአማሮ አካባቢዎች ዘንድሮን ጨምሮ ባለፉት አመታት ለ38 ሺህ 720 ደንበኞች ከ143 ሚሊዮን ብር በላይ በብድር በመስጠት ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲቆጥቡ ተደርጓል፡
፡በዚህ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 43 በመቶ ሴቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
በአለታ ወንዶ አካባቢ የተቋሙ ንዑስ ቅርንጫፍ ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ከምባታ እንዳስረዱት ደግሞ በግልና በማህበር ተደራጅተው የብድርና የሙያ ድጋፍ ተደርጎላችው ስራ ፈጥረው ከተሰማሩ 5 ሺህ 755 ደንበኞች እስካሁን ከ2 ነጥብ 7ሚሊዮን ብር በላይ በቁጠባ በመሰብሰብ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ከተቋሙ የአለታ ወንዶ አካባቢ ደንበኞች መካከል አቶ እንግዳ በየነና አቶ ሳሚ ፉጤ በሰጡት አስተያየት ከተቋሙ ባገኙት ብድር በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ እንዲሁም በሆቴልና መስተንግዶ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፎ ከ20 ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠራቸዉን ገልጠዋል ።
በተሰማሩበት ትርፋማ በመሆናቸዉ በአሁኑ ጊዜ ከ160 ሺህ ብር በላይ ከመቆጠብ ባሻገር አብዛኛዎቹ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን መብቃታቸዉን ተናግረዋል፡፡
የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ከተመሰረተበት ከ1989ዓም ጀምሮ እስካሁን በስሩ ባሉት 15 ዋናና 157 ንዑስ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለ470ሺህ 846 ደንበኞች ወደ ሶስት ቢሊዮን የሚጠጋ በብድር መሰጠቱንና አብዛኛው ግንዘብ ተመላሽ መደረጉን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊዉ አስታዉቀዋል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር