የሃዋሳ ከተማ ደኢህዴን ቅርንጫፍ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የኣመራር ሹም ሽር ተደረገ


የከተማው የደኢህዴን ጽህፈት ቤት ከዚህ በፊት በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት ካላ ሳሙኤል ሼባን ጨምሮ  ሌሎች ሁለት ኣመራራትን ከቦታቸው ኣንስቶ በምትካቸው ካላ ባጥሶ ዌጥሶን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ተክቷቸዋል።

እነዚህ ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተነሱት ካላ ሳሙኤል ሼባ ወደ ዞን የተዛወሩ ሲሆን የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ወደ ክልል መወሰዳቸው ተነግሯል።

ከስልጣን ላይ የተነሱት ሰዎች በምን ምክንያት እንደተነሱ ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም ከቅርብ ጊዜ ጅምሮ በሲዳማ ዞን ብሎም በሃዋሳ ከተማ ባለው የፖለቲካ ውጥረት ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ